
አቶ ተክለ ጆንባ
የቢሮ ኃላፊ መልዕክት
እንስሳት ለሲዳማ ሕዝብ ሁለንተናዊ የሀብት ምንጭ ነዉ፡፡ ይሁንና ከዚህ ሀብት ሕብረተሰባችን ማግኘት የሚገባዉን ያህል ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰዉ የእንስሳት ዝርያ ያለመሻሻል፣ ለእንስሳት የተማጣጠነ መኖ ያለመመገብ፣ ኋላቀር የአረባብ ዜዴ፣ የእንስሳት አያያዝ እና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ አለመዘመን ዋና ዋና ችግሮች ናቸዉ፡፡
ሲዳማ ክልል ሆኖ ከተደራጀ ወዲህ የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዘርፍ የሰጠዉ ትኩረት የተሻለ በመሆኑ ሕዝባችን ለእንስሳት እርባታ ስራ ከመነሳሳቱም በላይ የእንስሳት ምርት ፍላጎት በዓለም ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ በክልላችን ዉስጥም ዘርፉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየሰፋ መቷል፡፡ የእንስሳት ሀብት ልማት ገና ያልተጠቀምነዉ ሀብት በመሆኑ ይህንን ሀብት አዲስ ተክኖሎጅ ጥቅም ላይ በማዋል ከቻልን ክልላችንን በዚህ ዘርፍ ዉጤታማ ማድረግ እንችላለን፡፡
ስለሆነም ሕብረተሰባችን የእንስሳት ርቢን የከብት ብዛትና ቀንድ ከመቁጠር አልፎ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት ማርባት ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል የባለሙያ ምክር በመቀበል መሥራት፣ የእንሰሳትን ዝርያ ማሻሻልና ምርታማ የሆኑ የእንስሳት ዝርያን በመጠቀም ከቁጥር ይልቅ ከፍተኛ ምርት የሚያስገኙ ጥቂት እንስሳትን በተገቢዉ አያያዝ ማርባት ያስፈልጋል የሚል መልዕክት አለኝ፡፡
የእንስሳት ሀብታችን ለዕድገታችን!!
ዜና
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን የክልል ም/ቤት አባላት የተለያዩ የልማት ስራዎች በመጎብኘት ላይ ይገኛል። የካቲት 5/2016 ዓ.ም.
Sidaamu Dagoomu Qoqqowu Mootimma Saadate jiro Latishshi Biiro 2016 Bejetete Diri Maatete Jireenyi loossa 3kk Ruuwe 1kk agani mixote jeefishshi keeno Shoolente Zoonena Hawaasi Quchumi gashshooti…
The head of the Somali Region, Mr. Mustafe Muhammad, said that during the visit, the Lemat legacy works being carried out in the region are hopeful.
የምሰጡ አገለግሎቶች
ፎቶዎች
Facebook page
ራዕይ
በ2022 በገበያ ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሰፍኖ የአርሶ/አርብቶ/ አደሩ የኑሮ ደረጃ በመሠረታዊነት ተለውጦ ማየት፣
ተልዕኮ
የክልሉን እንስሳት እርባታ፣ የመኖ አቅርቦትና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ በማሻሻል፣ ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የእንስሳት ግብዓቶች እንዲቀርብና እንዲሰራጭ በማድረግ ምርትና ምርታማነት አድጎ፣የሕብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረገገጥ የሀገር ዉስጥ ገቢና የውጭ ምንዛሪ ማሳደግ፣
ዕሴቶች
ኅብረተሰቡን በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ተግባራት በንቃት እናሳትፋለን!
ለአርሶ አደሩ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን!
ሀብታችንን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን!
ሙያዊ ሥነ-ምግባርን እናሰፍናለን!