Head message

   

                                                                          አቶ ተክለ ጆንባ 

                                                                                                             የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

እንስሳት ለሲዳማ ሕዝብ ሁለንተናዊ የሀብት ምንጭ ነዉ፡፡ ይሁንና ከዚህ ሀብት ሕብረተሰባችን ማግኘት የሚገባዉን ያህል ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰዉ የእንስሳት ዝርያ ያለመሻሻል፣ ለእንስሳት የተማጣጠነ መኖ ያለመመገብ፣ ኋላቀር የአረባብ ዜዴ፣ የእንስሳት አያያዝ እና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ አለመዘመን ዋና ዋና ችግሮች ናቸዉ፡፡ 

ሲዳማ ክልል ሆኖ ከተደራጀ ወዲህ የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዘርፍ የሰጠዉ ትኩረት የተሻለ በመሆኑ ሕዝባችን ለእንስሳት እርባታ ስራ ከመነሳሳቱም በላይ የእንስሳት ምርት ፍላጎት በዓለም ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ በክልላችን ዉስጥም ዘርፉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየሰፋ መቷል፡፡ የእንስሳት ሀብት ልማት ገና ያልተጠቀምነዉ ሀብት በመሆኑ ይህንን ሀብት አዲስ ተክኖሎጅ ጥቅም ላይ በማዋል ከቻልን ክልላችንን በዚህ ዘርፍ ዉጤታማ ማድረግ እንችላለን፡፡

ስለሆነም ሕብረተሰባችን የእንስሳት ርቢን የከብት ብዛትና ቀንድ ከመቁጠር አልፎ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት ማርባት ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል የባለሙያ ምክር በመቀበል መሥራት፣ የእንሰሳትን ዝርያ ማሻሻልና ምርታማ የሆኑ የእንስሳት ዝርያን በመጠቀም ከቁጥር ይልቅ ከፍተኛ ምርት የሚያስገኙ ጥቂት እንስሳትን በተገቢዉ አያያዝ ማርባት ያስፈልጋል የሚል መልዕክት አለኝ፡፡

የእንስሳት ሀብታችን ለዕድገታችን!!

ዜና

Sidaamu Qoqqowu Mootimma Saadate Jiro Latishshi Biiro taaltino saadate sagale iillo halashshate haja la'anonsa bissa qinaabe loosate millimilote bare harsu.

The Sidama Regional Animal Resource Development Bureau has launched a mobilization with stakeholders to expand access to animal food.

የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የእንስሳት ምጥን መኖ ተደራሽነትን ለማስፋት ከባለድርሻ አካላት ጋሪ የተደረገ የንቅናቄ ተካሂዷል። ግንቦት 23/2016 ዓ.ም የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተክሌ ጆንባ የንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተዉ እንደ ድሮ ይሄን ያህል ከብት አለው ለመባልና…

Facebook page

    

ራዕይ  

በ2022 በገበያ ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሰፍኖ የአርሶ/አርብቶ/ አደሩ የኑሮ ደረጃ በመሠረታዊነት ተለውጦ ማየት፣

ተልዕኮ

የክልሉን እንስሳት እርባታ፣መኖ አቅርቦትና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ በማሻሻል፣ ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የእንስሳት ግብዓቶች እንዲቀርብና እንዲሰራጭ በማድረግ ምርትና ምርታማነት አድጎ፣የሕብረተሰቡን  ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረገገጥ የሀገር ዉስጥ ገቢና  የውጭ ምንዛሪ ማሳደግ፣

ዕሴቶች 

ኅብረተሰቡን በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ተግባራት በንቃት እናሳትፋለን!

ለአርሶ አደሩ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን!

ሀብታችንን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን!

ሙያዊ ሥነ-ምግባርን እናሰፍናለን!