
አቶ ተክለ ጆንባ
የቢሮ ኃላፊ መልዕክት
እንስሳት ለሲዳማ ሕዝብ ሁለንተናዊ የሀብት ምንጭ ነዉ፡፡ ይሁንና ከዚህ ሀብት ሕብረተሰባችን ማግኘት የሚገባዉን ያህል ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰዉ የእንስሳት ዝርያ ያለመሻሻል፣ ለእንስሳት የተማጣጠነ መኖ ያለመመገብ፣ ኋላቀር የአረባብ ዜዴ፣ የእንስሳት አያያዝ እና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ አለመዘመን ዋና ዋና ችግሮች ናቸዉ፡፡
ሲዳማ ክልል ሆኖ ከተደራጀ ወዲህ የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዘርፍ የሰጠዉ ትኩረት የተሻለ በመሆኑ ሕዝባችን ለእንስሳት እርባታ ስራ ከመነሳሳቱም በላይ የእንስሳት ምርት ፍላጎት በዓለም ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ በክልላችን ዉስጥም ዘርፉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየሰፋ መቷል፡፡ የእንስሳት ሀብት ልማት ገና ያልተጠቀምነዉ ሀብት በመሆኑ ይህንን ሀብት አዲስ ተክኖሎጅ ጥቅም ላይ በማዋል ከቻልን ክልላችንን በዚህ ዘርፍ ዉጤታማ ማድረግ እንችላለን፡፡
ስለሆነም ሕብረተሰባችን የእንስሳት ርቢን የከብት ብዛትና ቀንድ ከመቁጠር አልፎ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት ማርባት ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል የባለሙያ ምክር በመቀበል መሥራት፣ የእንሰሳትን ዝርያ ማሻሻልና ምርታማ የሆኑ የእንስሳት ዝርያን በመጠቀም ከቁጥር ይልቅ ከፍተኛ ምርት የሚያስገኙ ጥቂት እንስሳትን በተገቢዉ አያያዝ ማርባት ያስፈልጋል የሚል መልዕክት አለኝ፡፡
የእንስሳት ሀብታችን ለዕድገታችን!!
ዜና
Lemat's legacy is the importance of agriculture not only in accelerating economic growth, but also in supplementing the people's rich food supply and improving nutrition.
የሌማት ትሩፋት ግብርና የኢኮኖሚ እድገትን ከማፋጠን ባሻገር የህዝቡን የበለፀገ ምግብ አቅርቦት በሟሟላትና የአመጋገብ ስርዓትን በማሻሻል ረገድ የሚሰጠው ጠቀሜታ ላቅ ያለ ነው። እንደ ሀገር የሌማት ትሩፋት ግብርና ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶት መሠራት የጀመረው ከለውጡ መንግስት ወዲህ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከተጠበቀው…
The Sidama Regional Animal Resource Development Bureau has completed its two-day half-year plan for implementation of the Implementation Forum, setting out the…
የሲዳማ ክልል እንስሳት…
2017 B.Diri 6 aganni ripoortete keeno bare harisinota Sidaamu Dagoomu Qooqqowu Mootimma Saadate Jiro Latishshi Biiro xawissu.…
With their limited space in the city, as well as in housing yards, poultry and livestock, as well as beekeeping, and other legacies, the work of Lemat legacies can not
የምሰጡ አገለግሎቶች
ፎቶዎች
Facebook page
ራዕይ
በ2022 በገበያ ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሰፍኖ የአርሶ/አርብቶ/ አደሩ የኑሮ ደረጃ በመሠረታዊነት ተለውጦ ማየት፣
ተልዕኮ
የክልሉን እንስሳት እርባታ፣ የመኖ አቅርቦትና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ በማሻሻል፣ ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የእንስሳት ግብዓቶች እንዲቀርብና እንዲሰራጭ በማድረግ ምርትና ምርታማነት አድጎ፣የሕብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረገገጥ የሀገር ዉስጥ ገቢና የውጭ ምንዛሪ ማሳደግ፣
ዕሴቶች
ኅብረተሰቡን በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ተግባራት በንቃት እናሳትፋለን!
ለአርሶ አደሩ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን!
ሀብታችንን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን!
ሙያዊ ሥነ-ምግባርን እናሰፍናለን!