የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የገጠር ልማት መምሪያ ኃላፍዎች ከአዲሲ የቢሮ ኃላፍ ጋር የትውውቅና የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ግንገማና ውይይት መድረክ አካሄዱ።
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት
የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ፎና በትዉውቅ መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግራቸው የህዝባችን ታርካዊ አመጣጥ ስታይ ከእንስሳት ሀብት ልማት ጋር ተያያዥነት ያለዉ በመሆኑ አንስተዉ ህዝባችንን ከእንስሳት ሀብት ልማት ስራ ነጥለን መለየት አንችልም በማለት አብራርተዋል።
የቢሮ ኃላፊዉ አክለውም ይህ የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ቢሮ ሆኖ ከተደራጀበት ጊዜ ጀምሮ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዉ፣ የተመዘገበዉ ውጤት በብዙ ተለፍቶበትና ተሰርቶ የመጣ በመሆኑ በማንሳት ለወደፊትም ይሄንን ወጤት በማስቀጠል የቤተሰብ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደምቻል አስገንዝበዋል።
የሁሉም ዞን የገጠር ልማት መምሪያ ኃላፍዎች የቢሮ ኃላፊን እንኳን ደህና መጣህ መልዕክታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ አብረዉ በመተባበርና በመተጋገዝ እንድሁም በቅንነትና በታማኝነት አብረው በመስራት ከቀድሞ የተሻለውን ዉጤት ለማስመዝገብም ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊዎችና የማናጅመንት አካላት እንድሁም የአራቱም ዞንና የሀዋሳ ከተማ የገጠር ልማት መምሪያ ኃላፍዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
ለበለጠ መረጃ፣
https://www.facebook.com/share/1CfX954x6m/
Telegram: https://t.me/+R3huSpceCbdjYmQ0
https://chat.whatsapp.com/CBp85WlsTRA9RSzdigikOs
https://www.sldb.org.et/ANIMALS/