Skip to main content

       

  የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ስልጣንና ተግባር

1. የእንስሳት ሀብት (የቤት እንስሳት፣ ንብ፣ ዓሣና ወዘተ.) ልማት ዘርፍን ለማስፋፋት የሚረዳ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ህጎችን ያዘጋጃል፣ ሲፈቀዱም በሥራ ላይ መዋላቸዉን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ያስፈፀማል፡፡

2. የእንስሳት ሀብት ልማት ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በማዘጋጀት ይፈጽማል፣ ያስፈጽማል፣ ይከታተላል፣ የኤክስቴንሽን ሥረዓቱን በማጥናት እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡

3. በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ የእንስሳት ዝሪያዎችን በልማት ቀጠናዎች ይለያል፣ ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ይተገብራል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡

4. በክልሉ ዉስጥ ምርታማነታቸዉንና በሽታን በመቋቋም የታወቁ የእንስሳት ዝሪያዎችን ለመጠበቅ ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡

5. አስተማማኝ የእንስሳት መኖ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የተሻሻለ የመኖ ልማት ሥራዎችን ያከናውናል፣ ከተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ጋር አቀናጅቶ እንዲለማ ያደርጋል፤ ያስተባብራል፡፡

6. የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያ ግብዓት አቅርቦት ያመቻቻል፣ እንዲባዙም ያደርጋል፡፡

7. ክልል አቀፍ የእንስሳት በሽታ ቁጥጥር ስትራቴጂ ይነድፋል፣ ያስፈፅማል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

እርምጃ ይወስዳል፡፡

8. መከላከልን መሰረት ያደረገ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ይሰጣል፣ የእንስሳት በሽታዎች ምርመራ፤ አሰሳና ቁጥጥር ሥራዎችን ያካሂዳል፡፡

9. ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ የሥጋና የእንስሳት ተዋፅኦዎች ለህብረተሰቡ እንዲቀርቡ በቄራዎች የሥጋ ምርመራ እንዲካሄድ ያደርጋል፣ ደረጃቸዉን የጠበቁ ቄራዎች በገጠርና በከተሞች እንዲገነቡ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡

10. በተዋረድ ባሉ አደረጃጀቶች የእንስሳት ህክምና ክሊኒክ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

11. ለእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ልማትና ንግድ ለእንስሳት ህክምናና ክልኒክ አገልግሎት ለሚሰማሩ አካላት በወጡና በሚወጡ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶች መሰረት የብቃት ምዘና ያደርጋል፣ ማስረጃ ይሰጣል፣ በቅንጅት ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡

12. በክልሉ ዉስጥ የእንስሳት ንግድ የጉዞ መስመሮችን ይለያል፣ ማረፊያ ጣቢያዎች እንዲቋቋሙ ያደረጋል፣ የኳራንታይንና የፍተሻ ማዕከላትን በማደራጀት በክልሉ

 ዉስጥ፤ ከክልሉ የሚወጡና የሚገቡ እንስሳትን ይቆጣጠራል፣ ከአጎራባች ክልሎችና ከፌዴራል መንግስት አካላትጋር በትብብር ይሰራል፡፡

13. የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያና ማሻሻያ ግብዓቶች አቅርቦት ያመቻቻል፣ ያስተባብራል፡፡

14. የእንስሳት ሀብት ልማትና ጥበቃ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች እንዲቋቋሙና እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ በበላይነት ይመራል፤ ያስተዳድራል፡፡

15. በእንስሳት ሀብት ልማት ለተሰማሩ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮችና ባለሀብቶች ጥራትና ደረጃዉን የጠበቀ እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ እንዲያቀርቡና አገልግሎት እንዲሰጡ የአቅም ግንባታ ሥራና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፡፡

16. ከሚመለከታቸዉ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡ 17.የክልሉን የእንስሳት ሀብት ልማት መረጃ በዘመናዊ መልኩ ያሰባስባል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ ጥቅም ላይ እንዲዉል ያደርጋል፡፡

18. በእንስሳት ሀብት ልማት ላይ

ከሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች በማጣጣም እንዲስፋፋ ያደርጋል፤

19. ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡