Skip to main content
Head message

   

                                                                      አቶ ተክለ ጆንባ የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

እንስሳት ለሲዳማ ሕዝብ ሁለንተናዊ የሀብት ምንጭ ነዉ፡፡ እንስሳት በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ሀብት ብቻ ሳይሆን የዝናና የክብር  መገለጫ ተደርጎም ይወሰዳል፡፡ ገብ፣ የገንብ ምግብ መገኛ ፣ለእርሻ ስራ ዋነኛ አገልጋይና የተፈጥሮ ማዳበርያ ምንጭ ነዉ፡፡ የሲዳማ ህዝብ ለእንስሳት ካለዉ ክብርና ፍቅር በተነሳ ሰላምታ ስልዋወጡ ከልጆች በመቀጠል ስላም መሆናቸዉን የሚጠይቁት እንስሳትን ነዉ፡፡ይሁን እንጅ ከዚህ ሀብት ህዝባችን  የሚገባዉን ያህል ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱት መካከል፡-ባህላዊና ኃላ ቀር  የአረባብ ዘዴ፣ ዝርያ ያለመሻሻል፣ እንስሳት በቂ መኖ ያለመኖር የእንስሳት አያያዝ እና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ አለመዘመን ዋና ዋና ችግሮች ናቸዉ፡፡  ህዝባችን ከእንስሳት ጋር በጣም የጠበቀ ቁርጭትና ፍቅር ብኖረዉም ከዘርፉ ተጠቃም አለመሆኑን በቅጡ የተረዳዉ የክልሉ መንግስት ለዘርፍ በሰጠዉ ከፍተኛ ትኩረት ባለፉት ሁለት ዓመታት የተሻለ ስራ ተስርቷል፡፡ አመርቂ ዉጤትም ተመዝግቧል፡፡ ህዝባችን ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆንም ጀምሯል፡፡ አሁንም ቢሆን ካለን ዕምቅ ሀብትና ምቹ ሁኔታ አንጻር የእንስሳት ሀብታችንን ገና ያልተጠቀምነዉ በመሆኑ ይህንን ዕምቅ ሀብት በዘመኑ ተክኖሎጂ በማስደገፍ፣ ማልማትና ማርባት ከቻልን የለማና የበለጸገች ሲዳማን ማየት ሩቅ አይሆንም፡፡ለዚህም ላለፉት ሁለት ዓመታት ያስመዘገብነዉ ዉጠት ምስክር ነዉ፡፡ ስለሆነም ሕብረተሰባችን የእንስሳት ርቢን የከብት ብዛትና ቀንድ ከመቁጠር አልፎ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት ከባህላዊ አረባብ ወጥቶ በዘመናዊ እርባታ ዜደ ማርባት ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል የባለሙያን ምክር መስማትና መተግበር፣ የእንሰሳትን ዝርያ ማሻሻልና ምርታማ የሆኑ የእንስሳት ዝርያን መጠቀም በቂ መኖ ማልማትና ማዘጋጀት፣ከቁጥር ይልቅ ከፍተኛ ምርት የሚያስገኙ ጥቂት እንስሳትን በተገቢዉ አያያዝ ማርባት በእንስሳት ሀብት ልማት የቤተሰብን ብልጽግና  ለማረጋግጥ እንትጋ የሚል ጠንካራ መልዕክት አለኝ፡፡

 

የእንስሳት ሀብታችን ለዕድገታችን!!