አቶ ተክለ ጆንባ
የቢሮ ኃላፊ መልዕክት
እንስሳት ለሲዳማ ሕዝብ ሁለንተናዊ የሀብት ምንጭ ነዉ፡፡ ይሁንና ከዚህ ሀብት ሕብረተሰባችን ማግኘት የሚገባዉን ያህል ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰዉ የእንስሳት ዝርያ ያለመሻሻል፣ ለእንስሳት የተማጣጠነ መኖ ያለመመገብ፣ ኋላቀር የአረባብ ዜዴ፣ የእንስሳት አያያዝ እና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ አለመዘመን ዋና ዋና ችግሮች ናቸዉ፡፡
ሲዳማ ክልል ሆኖ ከተደራጀ ወዲህ የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዘርፍ የሰጠዉ ትኩረት የተሻለ በመሆኑ ሕዝባችን ለእንስሳት እርባታ ስራ ከመነሳሳቱም በላይ የእንስሳት ምርት ፍላጎት በዓለም ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ በክልላችን ዉስጥም ዘርፉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየሰፋ መቷል፡፡ የእንስሳት ሀብት ልማት ገና ያልተጠቀምነዉ ሀብት በመሆኑ ይህንን ሀብት አዲስ ተክኖሎጅ ጥቅም ላይ በማዋል ከቻልን ክልላችንን በዚህ ዘርፍ ዉጤታማ ማድረግ እንችላለን፡፡
ስለሆነም ሕብረተሰባችን የእንስሳት ርቢን የከብት ብዛትና ቀንድ ከመቁጠር አልፎ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት ማርባት ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል የባለሙያ ምክር በመቀበል መሥራት፣ የእንሰሳትን ዝርያ ማሻሻልና ምርታማ የሆኑ የእንስሳት ዝርያን በመጠቀም ከቁጥር ይልቅ ከፍተኛ ምርት የሚያስገኙ ጥቂት እንስሳትን በተገቢዉ አያያዝ ማርባት ያስፈልጋል የሚል መልዕክት አለኝ፡፡
የእንስሳት ሀብታችን ለዕድገታችን!!
ዜና
ክልል አቀፍ ዓሣ ቀን አየተከበረ እንደሆነና በዘርፉ ሰፊ ሥራዎች እየተሰራ እንደሆነ የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ። ሚያዝያ 22/2016 የቀኑ እንግዶች ዓሣን ቀን በማሰመልት በጓሮ ዓሳ ልማት የተሰሩ ሥራዎችን የጎበኙ ስሆን ባዩት ነገር ጥሩ ልምድ ልዉዉጥ እንደወሰዱም ተናግረዋል በዕለቱም ስለ…
Sidama regional animal resource development office has stated that the regional fishing day is being celebrated and extensive works are being done in the sector.
Sidama national regional government animal resource development office announced that it has built and started working in Sidama region animal health care laboratory. April 22/2016 E.C.
Sidamu Dagoomu Qoqqowi Motimma Sadate Jiro Latishshi Biiro Loonsanni hee’noonni lossa laisse xawishsha Uytu.
የምሰጡ አገለግሎቶች
ፎቶዎች
Facebook page
ራዕይ
በ2022 በገበያ ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሰፍኖ የአርሶ/አርብቶ/ አደሩ የኑሮ ደረጃ በመሠረታዊነት ተለውጦ ማየት፣
ተልዕኮ
የክልሉን እንስሳት እርባታ፣ የመኖ አቅርቦትና የእንስሳት ጤና አጠባበቅ በማሻሻል፣ ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የእንስሳት ግብዓቶች እንዲቀርብና እንዲሰራጭ በማድረግ ምርትና ምርታማነት አድጎ፣የሕብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረገገጥ የሀገር ዉስጥ ገቢና የውጭ ምንዛሪ ማሳደግ፣
ዕሴቶች
ኅብረተሰቡን በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ተግባራት በንቃት እናሳትፋለን!
ለአርሶ አደሩ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን!
ሀብታችንን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን!
ሙያዊ ሥነ-ምግባርን እናሰፍናለን!