
የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቅቋል::
ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም
የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸምን በአራቱም ዞን ማዕከላትና ሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር ግብርና መምሪያ ላይ የተሰሩ ሥራዎችን ለይተው የገመገሙ ስሆን በክልሉ የእንሳስት ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የቤተሰብ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራት በጥራትና በጥንካሬ ገምግመዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አስፋዉ ጎኔሶና የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዞን አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።
የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተክሌ ጆንባ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ተገኝተው የመረጃ ትክክለኛነትና ተአማኒነት ላይ ትኩረት ሰጥተው ማየት እንዳለባቸው የውሸት ሪፖርት እንዳይቀርብ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም አሰረድተዋል።
በተጨማሪም በዚህ ግማሽ ዓመቱ ውስጥ የተሰሩ ሥራዎችን በፓከጅ ለይ በዝርዝር የገመገሙ ስሆን በተለይም በዝርያ ማሻሻል በወተት ልማት በዶሮ ልማት በንብ ሀብት ልማትና እንዲሁም በዓሣ ሀብት ልማት ዕቅድ አፈጻጸም አመርቅ ዉጤት እንደተመዘገበና ህዝባችንም በዘርፉ ተጠቃሚ ያደረገ ሥራ እንደሆነም ገልጸዋል።
የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አስፋዉ ጎኔሶ በግምገማ መድረኩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የሁሉም ፖኬጅ ሪፖርት በዝርዝር መቅረብ እንዳለበትና የሌማት ትሩፋት ሥራ በተለየ መንገድ መታየት እንዳለበት ስራዉ ከክልሉ አልፎ በሀገር ደረጃ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለ ስሆን እንደ ቀድሞ ሳይሆን በተለየና ከዛም የተሻለ ዕቅድ ተይዞ መሰራት እንዳለበትም ገልጸዋል።
እንደ ክልል ከተጀመሩ የቤተሰብ ብልፅግና ማረጋገጫ ኢንቬቲቮች መካከል አንዱ የሆነው የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍን በውጤታማነት ለመፈፀም በትኩረት መስራት እንዳምገባና በዚህ ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች ያስመዘገቡ በመሆናቸው በቀጣይነትም የተሻለ ዕቅድ ተይዞ ለተሻለ ወጤት መስራት እንደምገባ ገልጸዋል።
በማጠቃለያም በዚህ በግማሽ ዓመት ውስጥ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም በማስዘገባቸው ለ4 ዞኖችና ለሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር እንድሁም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ግንባር ቀደም ወረዳዎች ቢሮው ለሥራቸው ይረዳቸውዋል ብሎ ሰላመነ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በሥራቸው ላይ ላሳዩት ታማኝነትና ታታሪነት ለወደፍት በተሻለ ሞራልና ቆራጥነት እንድሰሩ የማበረታቻ ሽልማትም አበርክቷል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዳይረክቶረት
ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ 🇪🇹