Skip to main content
tk

በሲዳማ ክልል ብቼኛ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶር አስገንብቶ ሥራ ማሰጀመሩን የሲዳማ ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የእንስሳት  ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ ። ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም ተቋሙ የኢፌዴሪ ግብርና ሚንስቴር የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ምኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅረ ረጋሳን ጨምሮ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የክልሉ እንስሳት ልማት ቢሮ ኃላፊዎችና የዞንና የወረዳ አሰተዳደሮች በተገኙበት  በይፋ ተመርቆ ወደ ሥራ ተገብቷል። ክልሉ ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት ያለበት በመሆኑ የእንስሳት ላብራቶሪ አሰፈላጊነት ከፍተኛ እንደሆኔ የተናገሩት የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳት ጤና ጥበቃና ግባት አቅርቦት ስርጭት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ሚልዮን ዮቴ የተለያየ ከእንስሳት ወደ ሰው የምተላለፍ በሽታን ለመከላከልም ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ዛሬ ተመርቆ ለስራ ክፍት የሆነው የእንስሳት ላብራቶሪ ብቼኛ የክልሉ እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ነው በማለት እንስሳት ላይ ለሚከሰቱ በሽታዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የላብራቶር አሰሳና ቅኝት በማድረግ አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት በላይ በሽታውን ከናካቴው ለማጥፋት ላቦራቶሪው ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑንም የሲዳማ ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የእንስሳት  ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተክሌ ጆንባ አሰረድተዋል ። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት የተጓደለውን ላቦራቶሪ ቁሳቁሶችን ለማሟላት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግም የኢፌደር መንግስት ግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሣ ተናግረዋል ። የእንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ  የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ ምርት ለማግኘት  ጉልህ ሚና እንደምኖረው በምረቃ መርሀግብር ላይ የተገኙ ታዳሚዎች ተናግረዋል። የሲዳማ ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የእንስሳት  ሀብት ልማት ቢሮ መንግሰት  ኮሙኒኬሽን ። ሀዋሳ ሲዳማ  ኢትዮጵያ 🇪🇹