Skip to main content
y

Lemat's legacy, through an effective development journey in the Sidama region, is playing a helpful role in turning into results the comprehensive efforts that we have started to overcome poverty at the family and community level by attracting the hopes of the youth, women, pastoralists and farmers, said the head of the Livestock Development Bureau of the Sidama Region. Mr. Tekle Jonba said.በሲዳማ ክልል የሌማት ትሩፋት ሥራዎች የቤተሰብ ብልፅግናን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በክልላችን በሚያስገርምና በሚያስደንቅ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ኃላፊው አክሎ ተናግሯል። በሲዳማ ክልል በሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጉብኝት ለይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባላትና የግብርና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በዳሌ ወረዳ በይርጋለም ከተማ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱም በክልሉ በሌማት ትሩፋት ስራ የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነትና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የቤተሰብ ብልፅግና ኅብረተሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን የክልሉ ምክር ቤት አባላትና የግብርና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በክልሉ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ተዘዋውሮ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በጉብኝቱም ላይ በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልን መፍጠር መቻሉን ተመልክተዋል ። በዶሮ እርባታ ፣ በከብት ማድለብ ፣ ንብ በማነብ እና በሌሎች የሌማት ትሩፋት ተግባራት ክልሉ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት በማስፋት የቤተሰብ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ በርካታ ሥራዎች መሰራቱን በጉብኝቱ ወቅት የተገኙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል። በጉብኝቱም ላይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባልና የግብርና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፍዎች እንዲሁም የክልሉ የዞንና ወረዳ የፊት አመራሮች በተገኙበት ጉብኝቱ ተካሂዷል። የካቲት 12/2016 ዓ.ም ሀዋሳ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ መግስት ኮሙኒኬሽን ። ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያዊ